ከትግራይ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተሰጠ መግለጫ

በሴራ ፖለቲካ የተጎነጎነ ነጭ ውሸት ማሰራጨት በውርደት ላይ ውርደት ከመጎንጨት የዘለለ አንዳችም ትርፍ የለውም

 የትግራይ ህዝብ እና መንግስት፣ የኦሮሞ ህዝብ የዘመናት መገለጫ የሆነው እና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ተቋም /ዮኔስኮ/ የተመዘገበው የኤሬቻ በዓል ዘንድሮም በተለመደው የአከባበር ስነ-ስርዓት እንዲከበር ከመፈለግ ውጪ ሌላ ዓለማም ሆነ ምኞት የላቸውም ፡፡

  ሆኖም በአሃዳዊዉና አምባገነኑ ቡድን የሚዘወሩ የፌደራል ሚድያዎች ባለፉት ሁለት ተኩል አመታት ሲያደረጉት የቆዩት ነጭ ውሸት የማሰራጨት አባዝያቸዉ፣ ትላንት መስከረም 21 /2013 ዓ/ም እንደተለመደው የትግራይ ፀጥታ ቢሮ ያሰማራቸው አሸባሪዎች ተይዘዋል በማለት የበሬ ወለደ ሃሰተኛ መረጃ አሰራጭተዋል፡፡

  ነገር ግን አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር፣ የትግራይ ህዝብ ወዶና ፈቅዶ የመረጣቸውን መሪዎችን ስም እያነሱ ጥላሸት ለመቀባት መፍጨርጨር ምናልባት የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሶቦችና ህዝቦች በአራቱም አቅጣጫዎች እያደረጉት ያለውን ትግል ለማኮላሸት ታስቦ ከሆነም ፈፅሞ የሚሳካ አይሆንም፡፡ ከዚህ ባሻገር “ሊበሏት የፈለጉዋት አሞራ ይሉዋታል  ዥግራ” እንደሚባለው በትግራይ ህዝብና መንግስት ላይ ሲካሄድ የነበረውን ብሄር ተኮር ጥቃት በትንኮሳ ለማስቀጠል የተጠነሰሰ እኩይ ሴራም ሆነ የትግራይ ህዝብ መሪዎች ስም በሴራ ፖለቲካ የተጎነጎነ ነጭ ውሸት ማሰራጨት በስልጣን ላይ ያለው አምባገነኑ ቡድን ዝቅጠት ከማሳየት እና በውርደት ላይ ውርደት ከመጎንጨት የዘለለ አንዳችም ትርፍ የለውም፡፡ ስለዚ ህዝባቸዉ በአግባቡና በሰላም እያስተዳደሩ ላሉት የትግራይ መሪዎች ስም የማብጠጠል እንቆቅልሽ ይቁም፡፡

 

ከትግራይ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

መስከረም 22/2013 ዓ/ም

መቐለ

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Show Buttons
Hide Buttons