በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ

የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቻይና ሻንሲ ግዛት ልኡካን ቡድን ወደ ትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኢንቨስትመንት፣ ትምህርት፣ መአድን ልማት እና የሁለትየሽ ግንኙነት ዙርያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ለማድረግ እየመጣ መሆኑን በግልፅ ደብዳቤ ለክልሉ መንግስት መፃፉ ይታወቃል፡፡

ሆኖም የትግራይ ክልል መንግስት እንግዶቹን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቆ በመጠበቅ ላይ እያለ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት ጉዞኣቸው እነዲስተጓጎል እና እንዳይመጡ ተደርጓል፡፡

በመሆኑም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የቻይና ሻንሲ ግዛት ልኡካን ቡድን ወደ ትግራይ እንዳይመጡ መከልከላቸው አግባብነት የሌለው መሆኑ በመግለፅ ፤ይህ ተግባር በትግራይ ክልል ውስጥ የሚደረጉትን የኢንቨስትመንትና ተዛማጅ የልማት እንቅስቃሴዎች በይፋ የሚገታና የህዝብ ለህዝብ መልካም ግንኙነት እንዳይጠናከር የማድረግ ተግባር የተፈፀመበትን ምክንያት በወቅቱ በቂ ማብራርያ እንዲሰጥበት የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን በይፋ የተሰጠ ማብራርያ ባለመኖሩ በድጋሚ ግልፅ ማብራሪያ እንዲሰጠው ይጠይቃል፡፡

የትግራይ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
መቐለ፡ ታህሳስ11 2012 ዓ/ም

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Show Buttons
Hide Buttons